የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት

የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት

image description

እንኳን ወደ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በደህና መጡ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ስር ካሉት 11 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አንዱ ሲሆን አመሠራረቱ እንደ እናት ተቋሙ እድሜ ጠገብና ባለ ታሪክ የሆነ ተቋም ነው ። ጽ/ቤቱ ከምስረታው ጀምሮ ለኤጀንሲው በአዋጅ የተሠጡትን ወሳኝ ኩነቶችን የመመዝገብና ማሥረጃ የመሥጠት ሀላፊነቶች በደረጃው ለኢትዩጵያውያን እና ለውጭ ሃገር ዜጎች ላለፉት ዓመታት አገልግሎት እየሰጠ ያለ ሲሆን በተልዕኮው እና በአደረጃጀት እንዲሁም በቴክኖሎጂ በርካታ ለውጦችን እያደረገ ዛሬ ላይ የደረሰ ተቋም ነው። ጽ/ቤቱ ለኤጀንሲው በ2018 ዓ.ም የሲቪል ምዝገባ ስርዓትን በተሟላ ሁኔታ እንድመራ ፣ እንድያደራጅ እና ምዝገባዎችን በየዕለቱ ተንትኖ ለከተማው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ውሳኔ አጋዥ መረጃ ማቅረብ እንድችል ሀላፊነት ሲሠጠው በደረጃው ሀላፊነቱን በመወጣት እና የተቋም ግንባታን በማረጋገጥ ከተማችን ላይ ወጥና የሚመሠገን የህዝብ አገልግሎት እንድገነባ የበኩሉን ሚና በመጫወት የድርሻውን የተወጣ ተቋም ነው። አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በስሩ 12 ቀጥተኛ አገልግሎት ሰጪ ወረዳዎች ያሉት ሲሆን ከ2015 ዓ.ም ተቋማዊ ሪፎርም እቅድ አቅዶ በሠራው የተቀናጀና ማህበረሰቡን ያሣተፈ የለውጥ ስራ 11 ወረዳዎችን ለአገልግሎት ምቹ አድርጎ በማደስ ተገልጋዩ በምቹ የአገልግሎት መሥጫ ቢሮዎች አገልግሎቱን እንድያገኝ እየሠራ ይገኛል ። በተጨማሪም ቅዳሜ ሙሉ ቀን በማገልገልና የአገልግሎት ክፍያን ሙሉ በቴሌ ብር እንድፈጸም በማድረግ እምርታዊ የአገልግሎት ለውጥ እንድመዘገብ አበክሮ የሠራ ተቋም ነው። በሌላ በኩል በክፍለ ከተማው የወቅታዊ ምዝገባ ሽፋን እንድያድግ በ10 የጤና ተቋማት ባለሙያ መድቦ ልደትና ሞትን እየመዘገበ ያለ ለህዝብ ቅርብ የሆነ እና አዳጊ የአገልግሎት ቅልጥፍና እያስመዘገበ ያለ በለውጥ ውስጥ ራሡን የሚያሣልፍ ጠንካራ ተቋም ነው።